Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል 400 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ዞኖች እየተጓጓዘ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ2016/17 የምርት ዘመን አገልግሎት ላይ የሚውል 400 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ዞኖች እየተጓጓዘ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

ለ2016/17 ምርት ዘመን በክልሉ 8 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ፍላጎት መኖሩን የቢሮው ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም 400 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ዞኖች እየተጓጓዘ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል።

እየገባ ያለው የአፈር ማዳበሪያ ዓይነትም÷ ‘ዩሪያ’ እና ‘ኤን ፒ ኤስ ፋሚሊ’ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

እየተጓጓዘ ካለው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ÷ 23 ሺህ ኩንታል ያህሉ ለኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ ለዩኒየኖችና ለአርሶ አደሮች ተደራሽ መደረጉን አረጋግጠዋል፡፡

እየገባ ያለው የአፈር ማዳበሪያ ለ2016/17 የመኸር ወቅት ብቻ ሳይሆን÷ አሁን በክልሉ በስፋት እየተካሄደ ለሚገኘው የበጋ መስኖ ልማት ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የአፈር ማዳበሪያውን በሚፈለገው መጠን ተደራሽ ከማድረግ ጎን ለጎን አርሶ አደሩ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ዝግጅቱ ላይ በስፋት እንዲተጋ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.