Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የ34 ዳኞችን ሹመት አጸደቀ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣስ 5 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የ34 ዳኞችን ሹመት በማጽደቅ የመጀመሪያ ጉባዔውን አጠናቋል።
 
ምክር ቤቱ የዳኞቹን ሹመት ያጸደቀው በአርባ ምንጭ ከተማ ላለፉት ሁለት ቀናት ያካሄደውን ጉባዔ ሲያጠናቅቅ ነው።
 
የክልሉ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ሰብሳቢና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቦጋለ ፈይሳ አምስት የዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና 29 የወረዳ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኞችን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
 
ጉባዔው በቀረቡ ዕጩ ዳኞች ዙሪያ የመከረ ሲሆን የሁሉንም ሹመት በሙሉ ድምፅ ማፅደቁን ኢዜአ ዘግቧል።
 
በተጨማሪም ምክር ቤቱ በዛሬ ውሎው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና ዋና ኦዲት ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ እንዲሁም የክልሉ ምክር ቤት የአሠራርና የአባላት ሥነ ምግባር ደንብና አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል።
 
ምክር ቤቱ ትናንት በነበረው ውሎ የክልሉ ምክር ቤት መስራች ጉባዔ ረቂቅ ቃለ ጉባዔን ጨምሮ የክልሉን ምክር ቤትና የክልሉ መንግሥት የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ እንዲሁም የአስፈጻሚ አካላትን ሹመትና በጀት ማጽደቁ ይታወሳል።
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.