Fana: At a Speed of Life!

118 ኢትዮጵያውያን ከታንዛንያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በታንዛንያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ118 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡

በዳሬ ሰላም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ታንዛንያ ከሚገኘው ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት እና ከሀገሪቱ የድንበር ቁጥጥርና አስተዳደር ኮሚሽን ጋር በመተባበር ነው ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት፡፡

ተመላሾቹ  በሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች ተታለውና ከፍተኛ ገንዘብ ከፍለው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሄድ በታንዛንያ የተለያዩ ክልሎች ሲገቡ በፀጥታ ሃይሎች ተይዘው ለእስር ተዳርገው መቆየታቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.