Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ክልል የቱሪዝም እንቅስቃሴን ዳግም የማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮሮና ወረርሽኝ እና በጦርነት ምክንያቶች ተቋርጦ የነበረውን የትግራይ ክልል የቱሪዝም እንቅስቃሴ ዳግም በይፋ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር በመቐለ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በጦርነቱ ወቅት ጥቃት የደረሰባቸውን ተቋማት መልሶ አገልግሎት ላይ ለማዋልና የክልሉን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ወደ ቀድሞ ለመመለስ የቱሪዝም ሚኒስቴር ከክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመሆን በይፋ አስጀምሯል።

በመርሐ ግቡሩ ላይም የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታዎች ስለሺ ግርማ እና ሌንሳ መኮንን ጨምሮ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ተገኝተዋል፡፡

እንዲሁም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አፅበሃ ገብረእግዚአብሄር (ዶ/ር)፣ የክልሉ የሐይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ የሆቴል ባለቤቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት መርሐ ግብሩ እየተካሄደ ነው።

በማህሌት ተ/ብርሃን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.