Fana: At a Speed of Life!

የፓን አፍሪካ ፓርላሜንት ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ትኩረቱን በሴቶች መብት ላይ ያደረገው 49ኛው የፓን አፍሪካ ፓርላሜንት ኮንፍረንስ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየተካሄደ ነው።

የሴቶችን መብት በማስከበርና የአመራር ብቃታቸውን በማሳደግ ተጽዕኖ ፈጣሪ አፍሪካውያን ሴቶችን ለማበረታታት ባለመው ኮንፍረንስ ላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች ኮከስ አባላት እየተሳተፉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የፓን አፍሪካ ፓርላሜንት ፕሬዚዳንት አሸብር ወ/ጊዮርጊስ (ዶ/ር)÷የኮንፍረንሱ ዓላማ የሴቶችን የውሣኔ ሰጪነት ሚና ለማጎልበት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከር መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የፓን አፍሪካ ፓርላሜንት የሴቶች ኮከስ ሰብሳቢ አሚና ቲዲያኒ ያያ በበኩላቸው÷በተለይ የአፍሪካውያን ሴቶች መብት አጠባበቅ ዙሪያ ያሉ የሕግ እና የፖሊሲ ክፍተቶችን ለመለየትና ለማረም ኮንፍረንሱ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ገለፃ አድርገዋል፡፡

በመድረኩ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሴቶችን መብት ለማስጠበቅና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል የተደረጉ ጥረቶችና ተሞክሮዎች በሚል የተዘጋጁ ጥናታዊ ጽሑፍ እንደሚቀርብ ተገልጿል፡፡

የፓን አፍሪካ ፓርላሜንት የሴቶች ኮከስ ሰብሳቢ አሚና ቲዲያኒ ያያ በበኩላቸው÷በተለይ የአፍሪካውያን ሴቶች መብት አጠባበቅ ዙሪያ ያሉ የሕግና የፖሊሲ ክፍተቶችን ለመለየትና ለማረም ኮንፍረንሱ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሴቶችን መብት ለማስጠበቅና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል የተደረጉ ጥረቶችና ተሞክሮዎች በሚል የተዘጋጁ ጥናታዊ ጽሑፎችም እንደሚቀርቡ ተመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያን የሚወክሉ የኮከሱ አባላት ከመድረኩ ልምድና ተሞክሮ የሚቀስሙበት ይሆናልም መባሉን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የፓን አፍሪካ ፓርላሜንት የሴቶች ኮከስ ከ54ቱ የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ ሴት የፖርላማ አባላትን የሚያቅፍ ነውም ተብሏል፡፡

በአፍሪካ የሥርዓተ ፆታ እኩልነትን ማስጠበቅ፣ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ማሳደግ ላይ ትኩረቱን በማድረግ የሴቶችን ፖለቲካዊና ማህበራዊ ተሳትፎ ለማሳደግም በመሥራት ላይ ይገኛል ነው የተባለው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.