Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና ተጠሪ ተቋማት የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች ማዕድ አጋርተዋል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካሞች ማዕድ አጋርቷል፡፡

በፕሮግራሙ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋ(ዶ/ር)÷ መንግስት የዜጎችን መሰረታዊ ፍላጎት ለማሟላት በሚያደርገው ጥረት በበዓላት የመደጋገፍ ባህል መጠናከር አለበት ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የጤና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል ማዕድ አጋርተዋል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ  ታደሰ ÷ሚኒስቴር መስሩያ ቤቱ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ በማድረግ ማዕድ ማጋራቱን ገልፀው ከማዕድ ማጋራቱ በተጨማሪ የፍራሽ፣ የንጽሕና መጠበቂያ፣ የመድኃኒትና ሌሎች ድጋፎች መደረጋቸውን  ገልጸዋል።

ለመቄዶንያ ከዚህ በፊትም የመድኃኒት፣ የአምቡላንስና ሌሎች ድጋፎች መደረጋቸውን ያስታወሱት ሚኒስትሯ ÷በቀጣይም የተጠናከረ ድጋፍ የሚደረግ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በተለይም ለአረጋውያን የመኖሪያ ቤትና የሕክምና አገልግሎት እየተገነባ የሚገኘው ሕንፃ እንዲጠናቀቅ የበኩላችንን ድጋፍ እናደርጋለን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.