Fana: At a Speed of Life!

ጥሪውን ተቀብለው ለሚመጡ እንግዶች ደቡብ ኢትዮጵያን ለማስጎብኘት ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 6 2016 (ኤፍ ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) በቅርቡ በውጭ ለሚኖሩ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ያቀረቡትን ጥሪ ተቀብለው ለሚመጡ እንግዶች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ መስኅቦችን ለማስጎብኘት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡

 ጉብኙቱን ምቹና ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል የማስፈጸሚያ ዕቅድ ተዘጋጅቶ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች መክረውበት መግባባት ላይ መደረሱን የክልሉ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ፍሬሕይወት ዱባለ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

 በዕቅዱ መሠረትም አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ አመላክተዋል፡፡

 በተጨማሪም ስለ ክልሉ የቱሪዝም ሐብቶች በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር እንዲያግዝ በአዲስ አበባ በሚካሄደው የኢትዮጵያ ሣምንት ላይ በመሳተፍ የክልሉን ቱባ ባሕልና እምቅ የቱሪዝም አቅም ለማስተዋወቅ  እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

 ከኢትዮጵያ ሣምንት ተሳትፎ ጎን ለጎንም በክልሉ የሚገኙ የመስኅብ ሥፍራዎችን ለማስጎብኘት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

 ለዚህም ወደ ክልሉ ለሚመጡ ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ልዩ አቀባበል ለማድረግ፣ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማስጎብኘት የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

 ከጎብኚዎቹ ጋር የፓናል ውይይት ለማድረግና የክልሉን የኢንቨስትመንት አማራጮች በአግባቡ ለማስተዋወቅ መታሰቡንም አመላክተዋል፡፡

 በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.