Fana: At a Speed of Life!

ኮሚሽኑ በአሜሪካና ካናዳ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአሜሪካ እና ካናዳ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በበይነ መረብ ተወያይቷል፡፡

በውይይቱም በተለያዩ የዓለማችን አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ሊኖራቸው ስለሚገባ ተሳትፎ እና ሊያደርጉ ስለሚገባቸው ድጋፍ ምክክር ተደርጓል፡፡

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በወቅቱ እንዳሉት÷ ባልተግባባንባቸው ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተመካክሮ መግባባት ለሀገራችን አስፈላጊ ነው፡፡

በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውን ለዚህ የበኩላቸውን ገንቢ አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚገባቸው መግለጻቸውንም የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ስለ ሀገራዊ ምክክር መሰረታዊ ፅንሰ-ሀሳብ፣ ኮሚሽኑ ስለሚከተለው የአሰራር ሥርዓትና እስካሁን ስላከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራትም ገለጻ ሰጥተዋል፡፡

ኮሚሽኑ በአሜሪካ እና በካናዳ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በትብብር ስለሚሰራባቸው መንገዶች የተለያዩ ምክረ-ሀሳቦች ከተሳታፊዎች መቅረባቸውም ተጠቅሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.