Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል የማዕድን ሃብት ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በትብብር ተጠንቶ ርክክብ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ማዕድን ቢሮ ከጎንደር ፣ ባሕር ዳር፣ ደብረ ብርሃን፣ ወሎ እና ወልድያ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር የክልሉን የማዕድን ሃብት አስጠንቶ ርክክብ ተካሂዷል።

የአማራ ክልል 80 በመቶ የቆዳ ስፋቱ የማዕድን ጥናት ያልተደረገለት መሆኑን የተናገሩት የቢሮው ም/ኃላፊ ታምራት ደምሴ፥ በዩኒቨርሲቲዎቹ የተደረገው ጥናት የክልሉን የማዕድን ጥናት ከ20 በመቶ ወደ 32 በመቶ ያሳድገዋል ብለዋል።

እስካሁን በጥናት የተለዩ 42 የከበሩና በከፊል የከበሩ፣ የኮንስትራክሽን፣ የኢነርጂ እና የኢንዱስትሪ ማዕድናት በክልሉ እንደሚገኙም ነው የገለጹት።

ማዕድን አዲሱ ክፍለ ኢኮኖሚ ሆኖ የእድገት ተስፋ የሚያመለክት በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ እንደሆነም ተነግሯል፡፡

በ2015 በጀት ዓመት ከ32 ሺህ በላይ ወጣቶች እንዲሁም በ2016 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 4 ሺህ 500 በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉ ተነስቷል።

ሁለት ዓመታትን የወሰደውን ጥናት ያስተባበሩት በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ዋና ጸሐፊ አስማረ ደጀኔ (ዶ/ር) እንዳሉት፥ ጥናቱ ከአሁን በፊት የማዕድን ክምችት፣ ስርጭት፣ ጥራትና የስነ ምድር ካርታ ጥናት ላይ ክልሉ የነበረበትን ክፍተት ይሞላል።

በዚህም በማዕድን ዘርፍ የሚሠማሩ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶችን ለመሳብና የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማስፋት በር ከፋች ነው ብለዋል።

በደሳለኝ ቢራራ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ (FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.