ፌዴራል ፖሊስ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጋር ተወያየ
አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ እና ከሌሎች የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል።
ኮሚሽኑ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ክልሎች ተንቀሳቅሰው የተሳካ ስራዎችን እንደሰሩ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አመራሮች ገልጸዋል።
በዚህም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ተገቢውን ድጋፍ እንዳደረገላቸውም አስታውሰዋል፡፡
በቀጣይም የሚካሄዱ የምክክር መድረኮች በሰላም እንዲካሄዱ ትብብሩ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መግለጻቸውን ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፥ ኮሚሽኑ በተለያዩ አካባቢዎች የሚያካሂዳቸው የምክክር መድረኮች ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲካሄዱ በትብብር ለመስራት በተደረገው ውይይት ላይ መስማማታቸውን ገልፀዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡ (FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Corporate S.C.)
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!