Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሠራዊት አባላት በደሴ ከተማ ታቦት የሚያልፍበትን መንገድ አጸዱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በደሴ ከተማ ታቦት የሚያልፍበትን መንገድ አጽድተዋል፡፡

በሥፍራው የሚገኘው ሬጅመንት ዋና አዛዥ÷ የጥምቀት በዓልን አስመልክቶ ሠራዊቱ የመዝገበ ምህረት ቅድስት ማርያም ታቦት የሚወጣበትን መንገድ ከህብረተሠቡ ጋር በጋራ ማጽዳቱን አንስተዋል፡፡

“እኛ ከህዝብ እንደወጣን ሁሉ የሕዝብ በዓላትን የመጠበቅ ግዴታ አለብን” ማለታቸውንም የከተማው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ዋና አዛዡ የመከላከያ ሠራዊት ከህብረብሔራዊ የተውጣጣና የህዝብ ስለሆነ ህብረተሠቡ ከመከላከያ ጎን ሊተባበር ይገባል ብለዋል።

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮችም ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.