የኢትዮጵያ አምባሳደሮችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዙሪያ ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ሀገራት ኢትዮጵያን እያገለገሉ የሚገኙ አምባሳደሮች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ ባህል፣ ጥበብና ስፖርት ለዲፕሎማሲ ስላላቸው ሚና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የብዝሃ ባህል ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ ይህንን ሃብቷንና ልዩ የሆነውን ባህሏን በማስተዋወቅ ገጽታዋን መገንባት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቷን ለማጠናከር መጠቀም እንደምትችል ተገልጿል።
በውጭ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች የባህል ልውውጥ መርሃ ግብር ፣ የሙዚቃ ፌስቲቫልና ስፖርታዊ ሁነቶችን በማዘጋጀት ረገድ አስተዋጽኦቸውን ሊያሳድጉ እንደሚገባ አቶ ቀጀላ ማስገንዘባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።