Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በካምፓላ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቅቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ልዑካቸው በዑጋንዳ ካምፓላ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቅቀው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እና የልዑካን ቡድናቸው በዑጋንዳ ካምፓላ በተካሄደው የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ ርዕሳነ ብሔር እና ርዕሳነ መንግሥታት 19ኛው ጉባዔ ላይ ተሳትፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግርም÷ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት ያለባቸውን ፈተና በተመለከተ አንስተዋል፡፡

የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት የሕዝብን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ ፈተናዎችን እየተጋፈጡ መሆናቸውንም አስገንዝበዋል፡፡

የባሕር በር የሌላት ኢትዮጵያም ችግሩን ለመፍታት በሰላማዊና በጋራ ተጠቃሚነት መርኅ መሰረት ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከጉባዔው ጎን ለጎን ባደረጓው የጎንዮሽ ውይይቶች÷ ከኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፣ ከሲሪላንካ ፕሬዚዳንት ራኒል ዊከርሜሲንጌ እና ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪንውሚ አዴሲና ጋር መክረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.