የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
የአሜሪካ ኤምባሲ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት ፥ በኢትዮጵያ የጥምቀት በዓልን ለሚያከብሩ የእምነቱ ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ ብሏል፡፡
የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በድምቀት እንደሚከበር ያወሳው ኤምባሲው ÷ በተባበሩት መንግሥታት ትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት(ዩኔስኮ) መመዝገቡንም አስታውሷል፡፡
በተመሳሳይ የሩሲያ ኤምባሲ ፥ የጥምቀትን በዓል ለሚያከብሩ የእምነት ተከታዮች በሙሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡
በዓሉ ለእምነቱ ተከታዮች የደስታ፣ የጤና እና የሰላም እንዲሆንም መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡
የእስራኤል፣ ብሪታንያ እና ስዊድን ኤምባሲዎች በበኩላቸው÷ የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት አንዱ መሆኑን በመጥቀስ ለእምነቱ ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡