Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ ፕሮጀክቶችን እየገነቡ ለሚገኙ ሰራተኞች ማዕድ አጋሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ በመዲናዋ ፕሮጀክቶችን እየገነቡ ለሚገኙ ሰራተኞች ማዕድ አጋርተዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ዛሬ የጥምቀት ዕለትን ጨምሮ ቀንና ሌሊት ያለ እረፍት ፕሮጀክቶችን እየገነቡ ካሉ ትጉህ ሰራተኞች ጋር ምሳ በጋራ በመብላት የጥምቀት በዓልን አክብረናል ብለዋል፡፡

የነዋሪውን የኑሮ ጫና ለማቅለልና የከተማዋን ገፅታ ለመቀየር የተጀመሩ ታላላቅ ፕሮጀክቶችና ሰው ተኮር ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜና በጀት በጥራት በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ እናደርጋታለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.