Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሠመሪታ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ረዳት ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ሠመሪታ ሰዋሰው ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ረዳት ዋና ዳይሬክተር ቫለሪ ጓርኒየሪ ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ በሚያከናውናቸው የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ተግባራት ዙሪያ ላይ መክረዋል፡፡

ተቋሙ ከኢትዮጵያ ጋር ባለው የረዥም ጊዜ ወዳጅነት መሠረትም÷ በሕይወት አድን እና ሰብዓዊ ድጋፍ ላይ ባከናወናቸው ሥራዎች ላይም ውይይ ማተኮሩን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም በምግብ ዕርዳታ አሰጣጥ ላይ በተደረጉ ማሻሻያዎች እና በቀጣይም ትኩረት ሊደረግባቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ተጠቅሷል፡፡

እንዲሁም እንደ ሀገር በተለያዩ ሰው ሠራሽ እና ተፈጥሯዊ ችግሮች ምክንያት የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት መጨመሩ ተገልጿል፡፡

የረድዔት ድርጅቶች እና መንግሥትም ይህን ታሳቢ ያደረገ ድጋፍ ማድረግ በሚቻልበት አግባብ በቅንጅት እንዲሠሩ በሚያስቸሉ ሁኔታዎች ላይ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.