4ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ነገ በቀጥታ ስርጭት ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2016 (ኤፍቢ ሲ) 4ኛው ፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር 3ኛ ሳምንት ነገ በቀጥታ ስርጭት ይካሄዳል።
የምዕራፍ 13፣ የምዕራፍ 14 እና የምዕራፍ 15 አሸናፊዎች አንድ ላይ በተገናኙበት በዚህ የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ነገ የምድብ አንድ 7 ተወዳዳሪዎች ከዛየን ባንድ ጋር በሁለት ዙሮች ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ።
በዚህኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ፋና ቴሌቪዥን ለመጀመሪያ ጊዜ አንደኛ ደረጃን ለሚያገኝ አሸናፊ የ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ሽልማት አዘጋጅቷል።
በአጠቃላይ ደግሞ የ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ሽልማት ነው የተዘጋጀው፡፡
ተሰጥኦ ኖሯቸው የተደበቁ ድምፃውያንን ወደ መድረክ ለማምጣት፣ የሙዚቃውንም ዘርፍ ለማበረታታት የራሱን ድርሻ እየተወጣ ያለው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሙያዊ ሥነ-ምግባር ያላቸው ድምፃውያን መድረክ እንዲሆን የበለጠ እንደሚሰራ ይታወቃል።
ይህን መሰረት ያደረገው 4ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ቅዳሜ በ3ኛ ሳምንት ውድድሩ ነገ 6 ሰዓት ላይ በፋና ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት መከታተል ትችላላችሁ።
በሙዚቃ ባለሙያዎች እና በተመልካቾች አጭር የጽሑፍ መልዕክት ዕለታዊ አቅርቦት ላይ ብቻ አተኩሮ የሚካሄደው 4ኛው የፋና ላምሮት የአሸናፊዎች አሸናፊ የድምፃውያን ውድድርን ተመልካቾች በ8222 የአጭር የጽሑፍ መልዕክት በመላክ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
በለምለም ዮሐንስ