ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በራስ አቅም ኦክስጅን ማምረት ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ሥር የሚገኘው ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በውስጥ አቅም ኦክስጅን ማምረት ጀምሯል፡፡
ሥራ በጀመረበት በትናንትናው ዕለት ብቻ 62 ኦክስጅን ማምረት መቻሉ ተገልጿል፡፡
በቀጣይም ሆስፒታሉ የማምረት አቅሙን በማጠናከር የኦክስጂን ፍላጎቱን ሙሉ ለሙሉ በራስ አቅም ለመሸፈን እንደሚሠራ ተመላክቷል፡፡
ሆስፒታሉ በቀን ከ120 እስከ 150 ኦክስጅን እንደሚያስፈልገውም ተጠቅሷል፡፡