ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከጣልያን ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከጣልያን ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አድሚራል ጁሴፔ ቻቮ ጋር ተወያዩ።
በጣልያን ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አድሚራል ጁሴፔ ቻቮ የተመራ ልዑክ መከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ሲደርስ በጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና በጀነራል መኮንኖች አቀባበል ተደርጎለታል።
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከጣሊያን ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አድሚራል ጁሴፔ ቻቮ ጋር ሁለቱ ሀገራት በወታደራዊ ትብብር ዙሪያ አብረው ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት አድርገዋል።
በሌላ መልኩም ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን መልካም ግንኙነት ማጠናከርና በጋራ መስራት በሚያስችላቸው ጉዳይ ዙሪያ ተወያይተዋል።