በአማራ ክልል በዘንድሮ የበልግ ወቅት ከ230 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በዘር ይሸፈናል ተባለ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በዘንድሮ የበልግ ወቅት ከ230 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በዘር እንደሚሸፈን ገለጸ፡፡
በቢሮው የሰብል ልማት ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ አግደው ሞላ÷ በሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች በዘንድሮ የበልግ ዘመን እስካሁን ከ29 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በተለያዩ ሰብሎች ተሸፍኗል ብለዋል፡፡
ከ200 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በድግግሞሽ መታረሱን የተናገሩት ዳይሬክተሩ፤ ከበልግ ወቅት እርሻ ከ4 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
በበልግ አዝመራው ከ300 ሺህ የሚልቁ አርሶ አደሮች እንደሚሳተፉ ገልጸው፤ የሚጥለውን ዝናብ በመጠቀም በልግ አብቃይ አርሶ አደሮች በፍጥነት ወደ ዘር ስራ መግባት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
በታለ ማሞ
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!