Fana: At a Speed of Life!

ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የከተሞች ፎረም ላይ ለመሳተፍ ወላይታ ሶዶ ገቡ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በ9ኛው የከተሞች ፎረም ላይ ለመሳተፍ ወላይታ ሶዶ ከተማ ገብተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተሩ ወላይታ ሶዶ ሲገቡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ ሌሎች የክልልና የዞኑ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት መሪዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አቶ ተመስገን በወላይታ ሶዶ ቆይታቸው በነገው ዕለት የሚጀምረው 9ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም መርሐ ግብር በይፋ ያስጀምራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከወላይታ ዞን አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወላይታ ሶዶ ከተማ የፎረሙን ዝግጅት በማጠናቀቅ እንግዶችን መቀበል ጀምራለች።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.