በሕክምና ዶክትሬት በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቁ መንትዮቹ ዶክተሮች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሕክምና ትምህርት ቤት በዛሬው ዕለት 271 የሕክምና ተማሪዎችን አስመርቋል።
ዩኒቨርሲቲው ካስመረቃቸው ተማሪዎች ውስጥም በሕክምና ዶክትሬት የተመረቁ መንትዮቹ ዶክተር ቸርነት ተስፋሁን እና ዶክተር ብሩክ ተስፋሁን ይገኙበታል፡፡
መንትዮቹ ዶክተሮች በከፍተኛ ማዕረግ እንደተመረቁም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲሰቲ መረጃ ያመላክታል፡፡