ሴቶችን ማስተማር መብታቸውን አውቀውና አስከብረው በነጻነት እንዲኖሩ የማድረግ ጉልህ ሚና አለው -ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ሴቶችን ማስተማር ተወዳዳሪ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማስቻሉም በተጨማሪ መብታቸውን አውቀውና አስከብረው በነጻነት እንዲኖሩ የማድረግ ጉልህ ሚና አለው ሲሉ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ተናገሩ፡፡
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ” እሷን አስተምሩ እና አፍሪካን ለውጡ” በሚል መሪ ቃል በ28ኛው የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች የልማት ድርጅት መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡
በንግግራቸው ÷ሴቶችን ማስተማር ተወዳዳሪ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማስቻሉም በተጨማሪ መብታቸውን አውቀውና አስከብረው በነጻነት እንዲኖሩ የማድረግ ጉልህ ሚና አለው ማለታቸውን ከቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ሴቶችን ለማስተማርና ለማብቃት የተሰሩ ስራዎችንም በመድረኩ አብራርተዋል፡፡