Fana: At a Speed of Life!

ለውጡ በክልሎች መካከል የነበረውን የሀብት ክፍፍል ቅሬታና አለመተማመን ፈትቷል – አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለውጡ በክልሎች መካከል የነበረውን የሀብት ክፍፍል ቅሬታና አለመተማመን መፍታት ችሏል ሲሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ።

ምክር ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በፌዴራል የመሰረተ ልማት ፍትሃዊነት ስርጭት አተገባበር ላይ ውይይት እያደረገ ነው።

በውይይቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር÷ ከለውጡ በፊት በክልሎች መካከል ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል ባለመኖሩ በህዝቦች መካከል የተፈጠረው አለመተማመን የግጭት መነሻ ነበር ብለዋል።

ነገር ግን ከለውጡ በኋላ ግልፅ የአሰራር ስርዓት በመተከሉ የነበረውን ቅሬታና አለመተማመን ማስወገድ ተችሏል ነው ያሉት።

ሆኖም ክልሎች የገቢ ምንጮቻቸውን አሟጠው በመጠቀምና የወጪ ቅነሳ ስርዓትን በመከተል ለውጤታማ የሀብት ክፍፍል የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በውይይቱ የፌዴራል መሰረተ ልማት ስርጭት ፍትሃዊነትን የተመለከተ የግምገማ ሰነድ ቀርቧል።

በዚህ የግምገማ ሰነድ መነሻነት በመወያየት የቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ የውይይቱ ትኩረት ስለመሆኑም ተመላክቷል።

በታሪኩ ለገሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.