Fana: At a Speed of Life!

የዓድዋ ድል ከራስ ፍላጎት ይልቅ የሀገር ፍቅር ቀድሞ የታየበት የአብሮነት እሴት ነው – አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓድዋ ድል ከራስ ፍላጎት ይልቅ የሀገር ፍቅር ቀድሞ የታየበት የአብሮነት እሴት ነው ሲሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ለ128ኛው የዓድዋ ድል በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም፤ የዓድዋ ድል የሀገር ፍቅር እና አንድነት ለስኬት እንደሚያበቃ ጎልቶ የታየበት ነው ብለዋል።

የዓድዋ ድል የመላ ጥቁር ህዝቦች የአሸናፊነት ተምሳሌት እንደሆነ ገልፀው፤ ድሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ምድር ቅኝ ገዢዎች በጥቁር ሕዝብ ተሸንፈው ኢትዮጵያውያን ለአፍሪካ የነፃነት አዲስ ምዕራፍ የከፈቱበት ታሪካዊ በዓል ነው ብለዋል።

የዓድዋ ድል ሁሉንም ኢትዮጵያውያን አንድ ከማድረግ ባለፈ ከራስ ፍላጎት ይልቅ የሀገር ፍቅር ቀድሞ የታየበት ትልቅ የአብሮነት እሴት እንደሆነ መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

የዓድዋ ድል መላው ጥቁር ህዝብ ለነጻነቱ እንዲነቃቃ ማድረጉን ገልጸው፤ ጀግኖች አባቶች የውጭ ወራሪን አሳፍረው በመመለስ የኢትዮጵያን ክብርና ነፃነት እንዳስጠበቁ ሁሉ የአሁኑ ትውልድም ህብረ ብሔራዊ አንድነቱን በማጠናከር ሀገርን ከድህነት ነፃ ለማውጣት በጽናት እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል።

የዓድዋ ድል በዓል ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ ያስከበረ አኩሪ ታሪክ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዓሉ ሲከበር እርስ በእርስ ያለውን አንድነት በማጎልበትና ሰላምን በማጽናት ሊሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.