Fana: At a Speed of Life!

በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ስኬታማ ውጤት ላስመዘገበው ልዑክ የእራት ግብዣ ተደረገለት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ስኬታማ ውጤት ላስመዘገበው ልዑክ በጋና የኢትዮጵያ ኤምባሲ የእራት ግብዣ እና የሽኝት መርሐ ግብር አከናውኗል፡፡

የእራት ግብዣ እና የሽኝት መርሐ ግብሩ ጋና አክራ በሚገኘው አቢሲንያ የኢትዮጵያ ሬስቶራንት ነው የተከናወነው፡፡

በመርሐ ግብሩ በጋና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ ፍቅሬ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር አትሌት ደራርቱ ቱሉና ሌሎች ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያ በጋና አክራ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው 13ኛው የመላ አፍሪካ የአትሌቲክስ ውድድር በ18 ሜዳሊያ ናይጄሪያን በመከተል 2ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል፡፡

በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የተሳተፈው 47 ወንድ እና 40 ሴት በድምሩ 87 አትሌቶችን የያዘው ልዑክም ነገ ምሽት አዲስ አበባ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡

በሰለሞን በቀለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.