Fana: At a Speed of Life!

በጅማና አጋሮ ከተማዎች የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)”ለሰላማችን ዘብ እንቆማለን ለውጡን እናስቀጥላን” በማለት በጅማና አጋሮ ከተማዎች የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

የድጋፍ ሰልፉ የጅማ ከተማና አካባቢዋ እንዲሁም የአጋሮ ከተማ ነዋሪዎች የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ለለውጡ ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።

ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ ሆና የሕዳሴን ግድብን ጨምሮ የሌሎች ግዙፍ ፕሮጀክቶች ግንባታ ሳይቋረጥ መከናወናቸውንና ይህም መንግስት ለልማት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም በለውጡ ማግስት የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት የፖለቲካ እስረኞችን ከመፍታት ጀምሮ በውጭ የነበሩ የፖለቲካ ኃይሎችን ወደ ሀገር እንዲመለሱ የተወሰደውን እርምጃ እንደሚያደንቁ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

በሙክታር ጣሃ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.