Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ  ከደቡብ ኮሪያጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጧን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ሰኔ 2 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ያላትን  ሁሉንም ግንኙነት  ከዛሬ ጀምሮ እንደምታቋርጥ አስታውቃለች።

ሰሜን ኮሪያ ለዚህም ምክንያት ያለችው ኑሯዋቸውን  በደቡብ ኮሪያ  ያደረጉ  የከዱኝ ዜጎች ጠብ አጫሪ መልእክቶችን  የያዙ በራሪ ወረቀቶችን በፊኛ በማድረግ ወደ እኔ በመላካቸው ነው ብላለች።

በዚህም ሰሜን ኮሪያ ደቡብ ኮሪያ ጠላቴ  ናት ከእርሷ ጋር ያለኝን ሁሉንም ግንኙነት ከዛሬ ጀምሮ አቋርጫለሁ  ይህ ደግሞ የመጀመሪያው እርምጃዬ ነውም ብላለች።

ሁለቱ  ሀገራት በ 2018 ከተወያዩ በኋላ ውጥረትን ለመቀነስ  በሰሜን ኮሪያ የድንበር ከተማ በሆነው ኬዝዮን ከተማ  የመገናኛ ቢሮ ከፍተው ነበር።

ይህ ሁለቱን ሀገራት የሚያገኛኘው ቢሮ ባለፈው ጥር ወር በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት  ለጊዜው ተዘግቶ የቆየ ቢሆንም  የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት  በስልክ ተጠብቆ ቆይቷል ፡፡

ይሁን እንጂ አሁን ሰሜን ኮሪያ  ከደቡብ ኮሪያ ጋር  ለመቀራረብ ተከፍቶ የነበረውን መስሪያ ቤት ከዛሬ ጀምሮ  እንደምትዘጋ አስታውቃለች።

ከዚያም ባለፈ በሁለቱ ሀገራት መሪዎች  መካከል የቀጥታ  የስልክ መስመር  ግንኙነት ጨምሮ ወታደራዊ  የግንኙነት መስመሮችም እንደሚቋረጡ  ባለስልጣናቱ  ተናግረዋል ፡፡

የሰሜን ኮሪያው መሪ እህት የሆኑት ኪም ዮ-ዮንግ ባለፈው ሳምንት በሰጡት መግለጫ÷ ደቡብ ኮሪያ  በሀገሯ የተቀመጡና  ሀገር የከዱ ቡድኖች በራሪ ወረቀቶች ወደ ሰሜን ከመላክ ካላቆመች በስተቀር የግንኙነት ቢሮውን እንደሚዘጋ አስፈራርተው ነበር ፡፡

ኪም ዮ-ዮንግ አክለውም  ጠብ አጫሪ መልዕክቶችን የታዙ ፊኛዎች ወደ ሰሜን ኮሪያ መላክ ሁለቱ ሀገራት በአውሮፓውያኑ 2018 ፓንሙጆም ላይ የደረሱበትን የሰላም ስምምነት የሚጥስና እኛንም የሚያበሳጭ ነው ብለው ነበር ።

በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረው ጦርነት በ1953 ቢያበቃም የሰላም ስምምነት ባለመፈራረማቸው ምክንያት እስካሁንም ጦርነት ላይ እንዳሉ ያስባሉም ነው የተባለው።

ምንጭ፡- ቢ.ቢ.ሲ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.