Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን የሚደግፍ የፕሮጀክት ስምምነት ከጃይካ ጋር ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና የጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን የሚደግፍ የፕሮጀክት ስምምነት ተፈራረሙ።

የፕሮጀክት ስምምነቱ ለአራት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ታምርት እንቅስቃሴን ተግባራዊ በማድረግ የአምራች ኢንዱስትሪን ተወዳዳሪነት ማሳደግ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ተጠቁሟል።

በዚህም የቴክኒካል፣ የፖሊሲ እና የአቅም ግንባታ ድጋፎች ይደረጋሉ ተብሏል።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ከተገኘው የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ የእውቀት፣ የክህሎት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ድጋፎች ከጃይካ እንደሚጠበቅ አመልክተዋል።

ይህም የእወቅትና የቴክሎጂ ሁኔታ በእድገትና ተወዳዳሪነት ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣል ብለዋል።

ጃይካን በመወከል ስምምነቱን የፈረሙት ኬንሱኬ ኡሺማ በበኩላቸው÷የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ውጤት እንዲያመጣ የእውቀት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የአቅም ግንባታ ድጋፍ እንደሚደያደርጉ ገልጸዋል፡፡

የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ፕሮጀክት ጽ/ቤትን፣ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሰማሩ የግል ባለሃብቶችና ማህበራትን እንደሚያጠናክር መገለጹን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.