1 ሺህ 181 ዜጎች ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶስት ዙር በረራ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን የመመለስ ስራ 1 ሺህ 181 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገለፀ፡፡
የተመለሱት ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ÷ 4ቱ እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
ለተመላሽ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ9 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተነግሯል።