Fana: At a Speed of Life!

ኬንያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙና ምልክት የማያሳዩ ህመምተኞችን ከሆስፒታል ልታስወጣ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ኬንያ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው የቫይረሱን ምልክት ያላሳዩ ህመምተኞችን ከሆስፒታሉ ልታስወጣ መሆኑን ገልጻለች ።

የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፊ ራሺድ አማን ÷በአገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ሁሉንም ታማሚዎች በሆስፒታሎች ውስጥ ማከም ከባድ ስለሆነ ውሳኔውን መተላለፉን ተናግረዋል።

በዚህም በቫይረሱ የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ያልደረሰና እና በቤታቸው ውስጥ ክትትል ማድረግ የሚችሉበት ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ታማሚዎች ከሆስፒታሉ በመውጣት በቤታቸው መቆየት እንደሚችሉ ተነግሯል ።

መንግሥት ታማሚዎቹ ከሆስፒታል የሚወጡበትን መመሪያ ማዘጋጀቱም ነው የተገለጸው።

በዚህም ታማሚዎቹ በቤታቸው ቢያንስ ለአስር ቀናት እራሳቸውን በመለየት የሚቆዩ ሲሆን ውሳኔውን ለማስፈጸምና ታማሚዎቹን ለመከታተል በማህበረሰብ ጤና ሰራተኞች የቤት ለቤት ክትትል እንደሚደረግላቸውም አስታውቋል፡፡

በምስራቃዊቷ ሃገር እስካሁን 3ሺህ 94 ሰዎች በኮሮናቫይረስ ተይዘዋል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.