የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በመላው የክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች እየተከበረ ነው።
በዓሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን፣ በካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን እና በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት÷ በስግደት፣ በጾም፣ በጸሎት እና በዝማሬ እየተከበረ ነው፡፡
በዕለቱ ቀኑን የሚያወሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የሚነበቡ ሲሆን፥ በዕለተ ስቅለት የተከናወኑ ተግባራት እየታሰበም ይሰገዳል።