Fana: At a Speed of Life!

ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን የመከላከልና መቆጣጠር ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ላይ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በወንጀል የተገኘን ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን የመከላከልና መቆጣጠር ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ላይ የተዘጋጀ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ተካሄደ፡፡

በምክክር መድረኩ የፍትህ ሚኒስትሩን ጌዲዮን ጤሞቲዎስን ጨምሮ ባለድርሻ የመንግስት ተቋማት፣ የፌደራል ፍርድ ቤት ዳኞች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ የህግ ምሁራን እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

በመድረኩ ላይ  የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ ÷ በኢትዮጵያ  ያለው የፋይናንስ ስርዓት ደህንነቱ የተጠበቀ ሆኖ እንዲመራ የረቂቅ አዋጁ መሻሻል አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም የረቂቅ አዋጁ መሻሻል የፋይናንስ ስርዓቱ  አለምአቀፋዊ ግዴታዎችን በሚያሟላ መልኩ በተቀረፀ ስርዓት ለመምራት የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በወንጀል የተገኘን ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣን አዋጅ ለማሻሻል አለም አቀፍ መለኪያዎችን እና ግዴታዎችን ማሟላት የሚገባው  በመሆኑ ለአዋጁ መሻሻል ምክንያቶች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

በመድረኩ የንብረት ማስመለስ እና ምንጩ ያልታወቀ ንብረት ይዞ መገኘትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ረቂቅ ህጎችም ቀርበው ውይይት የተካሄደባቸው መሆኑን ከገንዘብ ደህንነት አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.