Fana: At a Speed of Life!

ወጣቶች ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ ድጋፍ ይደረጋል- አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጣቶች ተደራጅተው ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ በወላይታ ዞን ዱጉና ፋንጎ ወረዳ በአርሶ አደሮችና በወጣቶች በኩታ ገጠም እየለማ የሚገኝን የበቆሎና ቦሎቄ ማሳ ጎብኝተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግርም ከምግብ ፍጆታ አልፈን ገበያን ለማረጋጋት ትርፍ ምርት ማምረት ይኖርብናል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

“ዱጉና ፋንጎ ወረዳ ቦቆሎና ቦሌቄ ሰጪ እንጅ ተመፅዋች አይሆንም” በሚል አቋም የተከናወነው ሥራ ለሌሎች አካባቢዎች ተሞክሮ እንደሚሆን ጠቅሰው÷ በሰብል ምርት የታየው ተነሳሽነት በሌሎች የልማት ሥራዎች እንዲደገም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በግብርና ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥተን ከሠራን በአጭር ጊዜ ብልፅግናን ማረጋገጥ እንደሚቻል በድጉና ፋንጎ ወረዳ በኩታ ገጠም እየለማ ያለው የቦቆሎ ሰብል አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

በክልሉ ያሉ ፀጋዎችን በአግባቡ በመለየትና በመጠቀም ከሠራን የሕዝቡን የኑሮ ሁኔታ መቀየር እንችላለን ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.