Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጽዱ ከተሞች ለኢትዮጵያ ከፍታ ንቅናቄ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጽዱ ከተሞች ለኢትዮጵያ ከፍታ ንቅናቄ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡

ንቅናቄውን የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው እና የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በቡታጅራ ከተማ አስጀምረውታል፡፡

በመርሐ ግብሩ የሌማት ትሩፋት፣ የመናፈሻ ፓርክ እና ሌሎች የመሰረተ ልማት ሥራዎች ጉብኝት መካሄዱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም በከተማው በአረንጓዴ ልማት የሚለሙ የመንገድ ዳርቻዎች መለየታቸው ነው የተገለጸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.