Fana: At a Speed of Life!

አቶ አሻድሊ ሀሰን ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተወያዩ።

በውይይቱ ርዕሰ መስተዳድሩ÷ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለህዝብ ሰላም እና ልማት ቅድሚያ ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ባለፉት ዓመታት በክልሉ ተከስተው በነበሩ የፀጥታ ችግሮ መሰረተ ልማቶችን ማውደማቸውን አስታውሰው÷ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሕዝቦች አንድነትን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ከመንግስት ጋር ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የሀሳብ ልዩነቶች ለዜጎች ሠላም እና ልማት እንቅፋት መሆን በማይችሉባቸው መንገዶች እጅ ለእጅ በመያያዝ የተጀመሩ የልማት፣ የመልካም አስተዳደር እና የሰላም ስራዎችን በፅኑ መሰረት ላይ ለማቆም ጥረት ሊደረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ለዚህም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ለክልሉ ህዝብ ሠላም እና ልማት ለማጎናፀፍ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከመንግስት ጋር በመቀራርብ ወንድማማችነትን ማረጋገጥ አማራጭ የሌለው መፍትሄ መሆኑም አመላክተዋል።

በክልሉ ያሉ እምቅ የተፈጥሮ ሃብቶችን ለልማት ማዋል የሚቻለው ተቀራርቦ በመስራት ሊሆን እንደሚገባ መግለፃቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.