Fana: At a Speed of Life!

249 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ከኩዌት ወደ አገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 249 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ከኩዌት ወደ አገራቸው ዛሬ ሰኔ 6 ቀን 2012 ዓም ተመልሰዋል።

ዜጎቻቸን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ዛሬ የመጡትን ጨምሮ እስካሁን በችግር ምክንያት በመጠለያ የነበሩ 748 ዜጎች ከኩዌት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተደርጓል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.