Fana: At a Speed of Life!

ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ 15 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የኮንትሮባንድ እቃው የቡታጅራ ከተማ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር ባደረጉት የተቀናጀ ክትትል ነው የተያዘው፡፡

የከተማዋ ፖሊስ አዛዥ ም/ኢንስፔክተር ሙሰማ ጀማል እንዳሉት÷ መነሻውን ሻኪሶ ደንቢዶሎ ያደረገው ኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ በወላይታ ሶዶ ሃላባ በኩል አቋርጦ ወደ ዝዋይ ለመግባት በጉዞ ላይ እንዳለ በቡታጅራ ከተማ ላይ ተይዟል፡፡

ተሽከርካሪው ለሕገ-ወጥ ኮንትሮባንድ ዝውውር ያመች ዘንድ ከፋብሪካው ስሪት ውጭ ተጨማሪ ድብቅና ምስጢራዊ ሻግ የተሰራለት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በተሽከርካሪው ሻግ ውስጥ 4 ሺህ 282 የሞባይል ስልኮች መገኘታቸውንም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.