Fana: At a Speed of Life!

አቶ እንዳሻው ጣሰው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን አስጀመሩ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ 3” በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደውን የ2016 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሆሳዕና ከተማ አስጀምረዋል፡፡

በዚሁ ወቅት አቶ እንዳሻው ጣሰው እንደገለጹት÷ በዘንድሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በ18 የትኩረት መስኮች ላይ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎች ይተገበራሉ።

በክልሉ እስከ 1 ቢሊየን ብር የሚደርስ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ይካሔዳል በማለት ገልጸው፤ በሚደረገው እንቅስቃሴ አመራሩ፣ ባለሀብቶች፣ ወጣቶች፣ መምህራን፣ የህክምና ባለሙያዎችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉ ገልፀዋል፡፡

በተያዘው ዓመት ከ2 ሺህ 500 በላይ የቤት ግንባታ እና እድሳት እንደሚካሔድ መጠቆሙን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.