1 ሺህ 174 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 174 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
የዛሬ ተመላሾች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ÷ ከእነዚህ ውስጥም ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ 17 ታዳጊ ህጻናት እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡