Fana: At a Speed of Life!

ለደቡብ ሱዳን ዲፕሎማቶች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 20 የደቡብ ሱዳን ዲፕሎማቶች በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትብብር የተዘጋጀላቸውን የሦስት ቀናት ስልጠና መርሐ-ግብር አጠናቀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በስልጠናው ማጠናቀቂያ ስነ-ስርዓት ላይ እንዳሉት ፥ ስልጠናው ዲፕሎማቶቹ በቀጣይ በስራቸው የሚያጋጥሟቸውን ውስብስብ ፈተናዎች ለመገንዘብና ለመፍታት ጠቃሚ ክህሎት እንዲኖራቸው ለማድረግ ታልሞ የተዘጋጀ ነው።

መሰል ስልጠናዎች በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን መካከል ያለውን የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ሚና ይኖራቸዋልም ብለዋል።

በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ አምባሳደር ናታሊና ኤድዋርድ ሙዩ ÷ ስልጠናውን ላዘጋጁት የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን አመስግነዋል።

በስልጠናው ማጠናቀቂያ ስነ-ስርዓትም ለዲፕሎማቶቹ ስልጠናውን በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቃቸው የምስክር ወረቀት እንደተበረከተላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.