Fana: At a Speed of Life!

ፍርድ ቤቱ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የነበሩ 88 ግለሰቦች ላይ የ14 ቀን ማጣሪያ ጊዜ ፈቀደ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፍርድ ቤቱ ከአማራ ክልል ወቅታዊ ጉዳይ ጋር ተያይዞ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የነበሩ 88 ግለሰቦች ላይ የ14 ቀን ማጣሪያ ጊዜ ፈቀደ፡፡

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መርማሪዎች በተለያዩ መዝገቦች ከአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የነበሩ 88 ግለሰቦችን በተለያዩ መዝገቦች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በማቅረብ ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ስራ ለማከናወን የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው÷ ተጠርጣሪዎቹ ከዚህ በፊት ታስረው መቆየታቸውን ጠቅሰው “ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሊሰጥ አይገባም ” በማለት የደንበኞቻቸው የዋስትና መብት እንዲፈቀድ ጥያቄ አቅርበዋል።

መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ÷ በአማራ ክልል ከደረሰው የሰውና የንብረት ጉዳት አንጻር ተጨማሪ ማስረጃዎችን የማሰባሰብ ስራ እንደሚቀረው ጠቅሶ የዋስትና ጥያቄያቸውን በመቃወም ተከራክሯል።

የግራ ቀኝ ክርክሩን የተከታተለውና የፖሊስ የምርመራ መዝገብን የተመለከተው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ከተጠረጠሩበት ወንጀል አንጻር ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት የተጠርጣሪዎችን ዋስትና ጥያቄ ለጊዜው በማለፍ ለፖሊስ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል።

በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.