4ኛው ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 4ኛው ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው።
“ምርምር ለከተማ ትራንስፎርሜሽን እና ዲጂታላይዜሽን” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ የሚገኘው ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ እንደተዘጋጀ ተገልጿል፡፡
ሀገርን ተወዳዳሪና ብቁ ለማድረግ የምርምር ውጤቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ፕሬዚዳንት ጣሰው ገብሬ (ዶ/ር) በመድረኩ መክፈቻ ላይ ተናግረዋል።
በመድረኩም የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎችና ባለድርሻ አካላትን ጨምሮ የዘርፉ ምሁራን ተገኝተዋል።
ዘመኑን የዋጁ አጋዥ ምርምሮች ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሁፎችም በኮንፈረንሱ ላይ እየቀረቡ ነው።
በአሸናፊ ሽብሩ