Fana: At a Speed of Life!

በወላይታ ሶዶ ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ሶዶ ከተማ ‘ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነትና ክብር’ በሚል መሪ ሀሳብ ከተማ አቀፍ ህዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ ፍቃዱ ተሰማ፣ የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ኤሌማ አቡበከር፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ረዳት የመንግስት ተጠሪ ዮሀንስ በየነ ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

መድረኩ በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችና እምቅ አቅሞችን በመጠቀም ከተረጂነት የተላቀቀ ህብረተሰብን መፍጠርን ዓላማ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

በፍቅርተ ከበደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.