ከ14 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ከውጭ መጓጓዙ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ሰኔ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ2016/17 የምርት ዘመን ከውጭ ከሚገዛው 19 ነጥብ 9 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 14 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ኩንታል ተጓጉዞ ወደብ መድረሱን የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡
ወደብ ከደረሰው ማዳበሪያ ውስጥ እስከ ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ 13 ሚሊየን 676 ሺህ 326 ኩንታል ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙ ተገልጿል፡፡
ማዳበሪያው አሁን ላይ በመሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካይት ለአርሶ አደሮች እየቀረበ መሆኑን ነው የኮሚሽኑ መረጃ ያመላከተው፡፡
በሌላ በኩል 1 ሚሊየን 228 ሺህ ኩንታል ተጨማሪ ማዳበሪያ የጫኑ ሁለት መርከቦች ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ጅቡቲ ወደብ እንደሚደርሱ ተጠቁሟል፡፡