Fana: At a Speed of Life!

ፊንላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር እንደምታጠናክር ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፊንላንድ ከኢትዮጵያ ጋር በንግድ እና ልማት ዘርፍ ያላትን ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ገለጸች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከፊንላንድ የውጭ ንግድና ልማት ሚኒስትር ቪሌ ታቪዮ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ተያያዥ ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ በትኩረት መክረዋል፡፡

አምባሳደር ምስጋኑ÷ፊላንድ በኢትዮጵያ በተለይም በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ንቁ ተሳትፎ እንድታደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ፊንላንድ ለኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ላደረገችው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ቪሌ ታቪዮ በበኩላቸው÷ፊንላንድ ከኢትዮጵያ ጋር በንግድና ልማት ዘርፍ ያላትን ትብብር ይበልጥ እንደምታጠናክር ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በቅርቡ የኢትዮ-ፊላንድ የጋራ የፖለቲካ ምክክር መድረክ ለማካሄድ መስማማታቸውም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.