Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የሥነ-ህንፃ እና የሥነ -ከተማ ዲዛይን ማዕከል እየተደራጀ ነው-ኢ/ር ታከለ ኡማ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በአዲስ አበባ የሥነ-ህንፃ እና የሥነ -ከተማ ዲዛይን ማዕከል እየተደራጀ መሆኑን ገልጸዋል።
 
ምክትል ከንቲባው በፌስቡክ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ÷”የአዲስ አበባን የከተማነት ጉዞ አበይት መልኮች እና የወደፊት ዕይታችንን ሻይ ቡና እያልን በእውቀት የምንመለከትበት እና የምንመካከርበት ትልቅ የሥነ-ህንፃ እና የሥነ -ከተማ ዲዛይን ማዕከል እያደራጀን ነው” ብለዋል።
 
“ቤት ሃሳብ ነው፣ የሠሪውን ሃሳብ ይመስላል÷ ከተማም ሃሳብ ነው፣ የከታሚዎቹን ሃሳብ እና ራዕይ ያክላልም ያሉት ኢንጂነር ታከለ አከታተሙ በአስተውሎት በሚመሩ ሰዎች ሲከናወን አስበው እንደሠሩት ቤት ይሞቃል፣ፍቅር እንደሞላበት መንደር ይደምቃል” ነው ያሉት።
 
አያይዘውም እንደ አዲስ አበባ ያለ አውራ ከተማ የአከታተም እና የዕድገት ሃሳብ የአገር እና የአህጉር ብሎም የአለም ኢኮኖሚ እና ፖለቲካ የሚዘወርበት መሆኑን መገንዘብ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
 
“ከተማ የሃሳብ ውጤት ነውና ቤታችንን እንደምንሠራ እያሰብን ከተማችንን እንገንባ” ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.