Fana: At a Speed of Life!

በ120 ሚሊየን ብር እየተገነባ ያለውን ቡርኪቱ ፊና ፕሮጀክት በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ መስኖና አርብቶ አደር ቢሮ ኃላፊ ግርማ ረጋሳ (ኢ/ር) በ120 ሚሊየን ብር እየተገነባ ያለውን ቡርኪቱ ፊና ፕሮጀክት በአጭር ጊዜ ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው አሉ፡፡

ውኃ አጠር በሆኑ አካባቢዎች የፊና ፕሮጀክቶች እየተገነቡ መሆኑን አመላክተው÷ ከነዚህ ውስጥ አራት ፕሮጀክቶች በምሥራቅ ቦረና ዞን እንደሚገኙ እና በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

ከፕሮጀክቶቹ መካከል በ120 ሚሊየን ብር እየተገነባ ያለውን ቡርኪቱ ፊና ፕሮጀክት በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

55 ሔክታር በማልማት 110 አባዎራዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የተገለጸው ቡርኪቱ ፕሮጀክት አርብቶአደሩ ውኃ እንዲያገኝ እና አምርቶ መጠቀም እንዲችል ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በታሪኩ ለገሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.