Fana: At a Speed of Life!

ዩኒቨርስቲዎች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የማህበረሰቡን የግንዛቤ ደረጃ ለማሳደግ እየሰሩ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 9 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀገሪቱ የሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የኮሮና ቫይረስ  ስርጭትን ለመከላከል የሚያግዙ  ግብአቶችን እያመረቱ ከማቅረብ ባለፈ የማህበረሰቡን የግንዛቤ ደረጃ ለማሳደግ  እየሰሩ  መሆኑን ከፋና ብሮድካስቲነግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ የዩኒቨርስቲ አመራሮች ገለጹ ።

የኮሮና ቫይረስ በሀገራችን ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጽያ የሚገኙ ከፍተኛ  የመንግስት የትምህርት ተቋማት የወረርሽኙን ስርጭት ለመከላከል የሚያስችሉ  ተግባራት በየፊናቸዉ እያከናወኑ ይገኛሉ ።

ከዚያም ባለፈ ዩኒቨርስቲዎቹ ለህክምናዉ ዘርፍ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለዉንና ህሙማንን ለመታደግ የሚያስችለዉን መካኒካል ቬንትሌተር በሰፊዉ ለማምረት የሚያስችል አቅም እየገነቡ መሆናቸዉን  ተናግረዋል።

ከፋና ብሮድካስቲነግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የጅማ እና የሰመራ ዩኒቨርስቲዎች  አመራሮች እንደገለፁት÷ በምርምር ስራዉ በኩል በተለይም የመተንነፈሻ ቬንትሌተሮችን ማምረት ላይም በቀጣይ ትኩረት እንደሚያደርጉ አስታዉቀዋል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ካደረጉ ዩኒቨስርቲዎች መካከል አንዱ የሰመራ ዩኒቨርስቲ ሲሆን ተቋሙ  የኢትዮ ጅቡቲ ድንበር አካባቢ እንደመገኘቱ መጠን በአሁኑ ሰአት ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑነ ከዉጭ ለገቡና  ለሌሎቸም  ዜጎች  ለይቶ ማቆያ በመሆን እገለገለ ይገኛል።

የዩኒቨርስቲዉ የምርምርና የማህበረሰብ  እንዲሁም የዩኒቨርስቲ ኢንደስትሪ ትስስር   ምክትል ፕሬዝደንት  ዶክተር አብዱህማን ከድር÷ዩኒቨርስቲያቸዉ የተለያዩ ግብአቶችን እያመረተ  ለማህበረሰቡ የማቅረብ ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል።

ዩኒቨርስቲው  በአካባቢዉ ያሉት የኳራንታይኖች ተመሳሳይ እና የተደራጀ  መረጃ  እንዲኖራቸዉ የሚያደርግ    የተቀናጀ የኮሮና ቋት የዳታ ቤዝ  ማዕከል እንዲኖር የሚያስችል ተግባር እያከናወነ  እንደሚገኝ ተገልጿል።

ከዚያም ባለፈ ዩኒቨርስቲው በጂፒኤስ የታገዘ   በአፋርኛና አማርኛ  የተዘጋጀ የኮሮና ቫይረስ ተጋላጭነትን የሚያመላክት የሞባይል መተግበሪያ አፕልኬሽንም የመጨረሻዉ ምእራፍ ላይ እንደደረሰ ምክትል ፕሬዝደንቱ ነግረዉናል።

ከተቋሙ ባሻገር መምህራኑም የተለያዩ የድጋፍ ስራዎችን እያካሄዱ መሆናቸዉን የገለፁት ምክትል ፕሬዝደንቱ÷  ማህበረሰቡን የማንቃትና የማስተማር ስራዉ  አሁንም በከፍተኛ ደረጃ በዩኒቨርስቲዉ ሙህራን ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል።

የጅማ ዩኒቨርስቲም የማህበረሰቡን ንቃተ ህሊና የማሳደግና የመከላከያ መንገዶችን በዙሪያዉ ለሚገኙ የማህበረሰቡ ክፍሎችን  ከማሳወቅ ባለፈ የወረርሽኙን ስርጭት  ለመመከት የሚያስችሉ ቁሳቁሶችን  እያመረተ መሆኑን የዩኒቨርስትዉ  ሜዲካል  ሴንተር ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አህመድ ሙሀመድ  ለጣቢያችን አስረድተዋል

ሁሉም የሀገሪቱ ዜጋ እራሱንንና ቤተሰቡን ከዚህ አስከፊ ወረርሽኝ በመጠበቅ  ማህበረሰቡንና  ሀገሩን ከሞትና ከዉድቀት የመታደግ ሀላፊነቱ በጥንቃቄ ሊወጣ እንደሚገባም የዩኒቨርስቲ አመራሮቹ ጥሪ አቅርበዋል።

በሙሀመድ አሊ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.