Fana: At a Speed of Life!

“መስፈርት አላሟሉም” የተባሉ 41 ትምህርት ቤቶች ፈቃድ ተሠረዘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “የሚጠበቅባቸውን መስፈርት አላሟሉም” የተባሉ 41 ትምህርት ቤቶች ፈቃድ መሠረዙን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ፈቃዳቸው የተሠረዘው የትምህርት ፖሊሲውን ባለመጠበቅና መስፈርቱን ባለማሟላታቸው ነው ብሏል ባለስልጣኑ፡፡

ባለስልጣኑ በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን መዝግበው የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶችን እና ፈቃዳቸው የተሠረዘ የትምህርት ተቋማትን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህም በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን መዝግበው የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች 1 ሺህ 332 ሲሆኑ÷ የማስተማር ፈቃድ እንደተሰጣቸውም ገልጿል፡፡

በሌላ በኩል 43 ትምህርት ቤቶች በራሳቸው ጊዜ መቀጠል ስላልቻሉ ፈቃዳቸው ተሠርዟል መባሉን የባለስልጣኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

እንዲሁም 150 ትምህርት ቤቶች ጉዳያቸው በሂደት ላይ መሆኑና  ወደፊት እንደሚገለጽ ተጠቁሟል፡፡

41 ትምህርት ቤቶች ደግሞ የትምህርት ፖሊሲውን ባለመጠበቅና መስፈርቱን ባለማሟላታቸው ፈቃዳቸው መሠረዙን ነው ባለስልጣኑ ያስታወቀው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.